ክርስቲያኖች ዒሳ ዓለይሂ ሰላምን በተመለከተ ወሰን እንዳለፉት ሁሉ ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ህዝባቸው እሳቸውን በማሞገስ በኩል፣ በአላህ ባህሪያትና ልዩ ድርጊቶቹ እሳቸውን በመግለፅ፣ የሩቅ እውቀትን እንደሚያውቁ በመሞገት፣ ወይም ከአሏህ ጋር እሳቸውን በመማፀንና በመሳሰሉት መልኩ ወሰን እንዳይታለፍባቸው አስጠነቀቁ። ከዚያም ከአሏህ ባርያዎች መካከል አንዱ መሆናቸውን ገልፀው፤ እሳቸውን "የአሏህ ባርያውና መልዕክተኛው" ብለን እንድንገልፃቸው አሳሰቡ።