ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከእሳት ነዋሪዎች መካከል እሳት ከገባ በኋላ ዝቅተኛውን ቅጣት ለሚቀጣው አላህ እንዲህ እንደሚለው ተናገሩ: ላንተ ዱንያና በውስጧ ያሉ ነገሮች ሁሉ ቢኖሩህ ከዚህ ቅጣት ፋንታ እነርሱን ፍዳ አታደርጋቸውምን? እርሱም: አዎን ይላል። አላህም እንዲህ ይለዋል: በአደም ጀርባ ሳለህ እኔ ካንተ ጋር ቃልኪዳን ስወስድ የፈለግኩትና ያዘዝኩህ ከዚህም የቀለለውን ነገር ነበር። እርሱም በኔ አንዳችንም አታጋራ የሚል ነበር። አንተ ግን ወደ ዱንያ ያመጣሁህ ጊዜ ማጋራትን እንጂ እምቢ አልክ።