ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተለለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን በምልጃቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እድለኛ የሚሆኑት "ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት" ማለትም ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው እንደሌለ አምነው ከሽርክ ይሁን ከይዩልኝና ይስሙልኝም ጥርት ያሉት መሆናቸውን ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አኼራ ላይ ሸፋዓ (ምልጃ) እንደሚያደርጉ ጸድቋል። ምልጃቸውም ተውሒድ ላላቸው ሰዎች ብቻ ነው።
  • የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሸፋዓ (ምልጃ) ተውሒድ ላይ እያለ (በኃጢዓቱ ምክንያት) ጀሀነም የተፈረደበትን ወደ ጀሀነም እንዳይገባ፤ ከገባ ደግሞ እንዲወጣ የሚያደርጉት ምልጃ ነው፤
  • ለአላህ ጥርት ተደርጋ የተባለች የተውሒድ ቃል ያላት ትሩፋትና የምታሳድረውን ከፍተኛ ተጽዕኖ እንረዳለን።
  • የተውሒድ ቃል የሚረጋገጠው ትርጉሟን በማወቅና የምታስፈርደውን ተግባራዊ በማድረግ ነው።
  • አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - ያላቸውን ደረጃና በዕውቀት ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።