አንድ የገጠር ሰው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ትንሳኤ ስለምትከሰትበት ወቅት ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: ለርሷ ከመልካም ስራ ምን አዘጋጅተህላታል? አሉት። ጠያቂውም: እኔ አላህና መልክተኛውን እወዳለሁ እንጂ ትልቅ ስራ አላዘጋጀሁላትም አለ። ከዚህ በቀር የቀልብም፣ የአካልም ሆነ የገንዘብ አምልኮ አላወሳም። እነዚህ ሁሉ ውዴታን ተከትሎ የሚመጡ ቅርንጫፎች ናቸውና። ለመልካም ስራ የሚያነሳሳውም እውነተኛ ውዴታ ስለሆነ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ: አንተ ጀነት ውስጥ ከወደድካቸው ጋር ነህ አሉት። የነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦች በዚህ ብስራት ከፍተኛ ደስታን ተደሰቱ። አነስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀጥሎ ስራው እንደነርሱ አምሳያ ባይሆንም እንኳ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን ስለሚወድ ከነርሱ ጋር መሆንንም ተስፋ እንደሚያደርግ ተናገረ።