ከአነስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።