ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች ተጠበቁ: የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ በአንተ እጠበቃለሁ!) ከሃይማኖታዊም ከአለማዊውም ፀጋህ መወገድ በአንተ እጠበቃለሁ፤ በእስልምና ላይ መፅናትንና ፀጋን የሚያስወግድ ከሆነ ወንጀል ላይ ከመውደቅም መራቅን እጠይቅሃለሁ። ሁለተኛው: (ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ) ወደ መከራ ከመለወጥ ማለት ነው። ዘውታሪ ደህንነትንና ከሁሉም በሽታዎችና ህመሞች ሰላም መሆንን እጠይቅሃለሁ። ሶስተኛው: (ከድንገተኛ መከራህ) ከባድ አደጋ ወይም መዐት ማለት ነው። መከራና ቅጣት በድንገት የመጣ ወቅትና ለተውበትና ለመመለስ ጊዜ ከሌለ ለተፈተነበት ሰው መከራው ትልቅና አደገኛ ይሆናል። አራተኛው: (ከአጠቃላይ ቁጣህ) ለቁጣህ የሚያስገድዱ ከሆኑ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ የተቆጣህበት ሰው በርግጥም ባዶ ቀረ ከሰረ ማለት ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠቅላይ የሆኑ ቃላትን የተጠቀሙት የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁጣ ምክንያቶች የሆኑትን ንግግሮች፣ ተግባሮችና እምነቶችን በሙሉ እንዲያጠቃልል ነው።