ጠቅላይ ከሆኑት የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓዎች መካከል ይህ አንዱ ነበር: "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ" ሀጢዐቴን "አለማወቄንም" ያለ እውቀት ከኔ የተከሰተውንም ወንጀል ማረኝ። "በሁሉም ነገሬ ወሰን ማለፌንም" ከልክ ማለፌንም ማጓደሌንም ማረኝ። "አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ።" አንተ አውቀኸው እኔ የረሳሁትን ማለት ነው። "አላህ ሆይ! ወንጀሌንና ሆን ብዬ የሰራሁትን ማረኝ" ወንጀልነቱን አውቄና ሆን ብዬ የሰራሁትንም ማረኝ። "ምሬንም ቀልዴንም" በቀልድ የሰራሁትንም በሁለቱም ሁኔታ ላይ ሆኜ የሰራሁትንም ማረኝ። "ይህ ሁሉ ከኔ ነው።" የተጠቀሱት ወንጀሎችና ነውሮች ቢሰበሰቡ ከኔው ናቸው። "አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን ወንጀል ማረኝ!" ያለፈውን "ያዘገየሁትንም ማረኝ" ለወደፊት የምሰራውን ማረኝ። "የመሰጠርኩትንም" የደበቅኩትን "ግልፅ ያወጣሁትንም" ይፋ ያወጣሁትን ማረኝ። "አንተ አስቀዳሚ ነህ! አንተም የሚያዘገይ ነህ!" ከፍጥረትህ የፈለግከውን ወደ እዝነትህ በመግጠምህም ለምትወደው ነገር ታስቀድማለህ። አንተ የፈለግከውንም ሰው እርሱን በማዋረድ ከነዚህ ነገሮች ታዘገየዋለህ። ከነገሮች ያዘገየኸውን የሚየስቀድም፣ ያስቀደምከውንም የሚያዘገይ የለም። "አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ችሎታው የተሟላ፣ ፍላጎቱ የተሟላ፣ ለምትሻው ነገር ሁሉ ፈፃሚ ነህ ማለት ነው።