ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለመሙላት የተላኩለት የሆነውን የመልካም ስነምግባር መሰረቶችን የሰበሰበች ዱዓ አደረጉ። እነርሱም: የሃይማኖት፣ የዱንያና የመጨረሻው አለም መስተካከል ናቸው። በነዚህ አጠር ባሉ ቃላቶች የነዚህን ሶስቱንም ያጠቃለለ ጥቅምን አከታትለው ለመኑ። በቅድሚያ በሃይማኖት መስተካከል ጀመሩ። የሁለቱም ሀገሮች ሁኔታ የሚስተካከሉት በርሱ ነውና። እንዲህ አሉ: (አላህ ሆይ! ሃይማኖቴን አስተካክለው።) በተሟላ መልኩ ስነስርዓቱን ጠብቄ እንድቆም ወፍቀኝ (አሳካልኝ)። (የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን) የጉዳዮቼ ባጠቃላይ ጠባቂ የሆነው ሃይማኖቴ ከተበላሸ ጉዳዮቼ ባጠቃላይ ይበላሻል፤ ባዶዬን እቀራለሁ፣ እከስራለሁ። እንዲስተካከል የተፈለገው የሃይማኖት ጉዳይም ዱንያ ስትስተካከል ካልሆነ በቀር ስለማይስተካከል እንዲህ አሉ: (ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) የሰውነት ጤና፣ ደህንነት፣ ሲሳይ፣ መልካም ሚስት፣ ጥሩ ዘር፣ ሐላል የሆነና አንተን ለማምለክ የሚያግዘኝን የሚያስፈልገኝን በመስጠት (ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) ቀጥለው ዱንያቸው እንዲስተካከል የጠየቁበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ጠየቁ: (በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን) የኑሮዬና የህይወት ዘመኔ ስፍራ የሆነውን። (መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለም አስተካክልልኝ።) አንተን ለመገናኘት የምመለስበት የሆነውን ማለት ነው። መጨረሻ የሚያምረውም ስራን በማስተካከልና አላህ ባሪያውን ለአምልኮ፣ ለኢኽላስና ለመልካም ፍፃሜ በመግጠሙ ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጪው አለምን ከዱንያ በኋላ ያስከተሉት የመጀመሪያው አለም ለሁለተኛው አለም መስተካከል መዳረሻ ስለሆነ ነው። ዱኒያው አላህ በፈለገው መልኩ የተስተካከለለት ሰው መጪው አለምም ለርሱ ይስተካከልለታል በርሷም ውስጥ ይደሰታል። (ህይወቴን አድርግ) የእድሜዬ መርዘምን (በሁሉም በኩል መልካም ነገር የምጨምርበት) መልካም ስራን የማበዛበት (ሞቴን አድርገው) መፍጠኑን (ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት) ሞትን ከፈተናዎች፣ ከመከራ፣ የወንጀልና የዝንጉነት ፈተና ላይ ከመውደቅ፣ ከዱንያ ችግርና ጭንቀት የምገላገልበትና እረፍትን የማገኝበት አድርገው።