የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አጎት የሆኑት ዐባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የሚጠይቁበት ዱዓ እንዲያስተምሯቸው ፈልገው መጡ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ በዲንም፣ በዱንያና በመጪው አለምም ከሚያጋጥሙ መከራና ነውር ደህናና ሰላም እንዲያደርጋቸው እንዲጠይቁ አስተማሯቸው። ዓባስም እንዲህ አሉ: ከቀናት በኋላ በድጋሚ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን የምጠይቅበት አስፈላጊ ዱዓ እንዲያስተምሩኝ ልጠይቅ ተመልሼ መጣሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ውዴታን በማሳየት "ዓባስ ሆይ! የአላህ መልክተኛ አጎት ሆይ! በዱንያና በመጪው አለም ሁሉንም ጉዳት እንዲከላከልልህና ሁሉንም መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሰጥህ አላህን ደህንነት እንዲሰጥህ ጠይቀው።" አሉት።