ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ ያበዙ ነበር። ከነርሱም መካከል: "አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር" የሚለው ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው አለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው። ይህ ዱዓ ጣፋጭ፣ ሰፊና ሐላል የሆነ ሲሳይን፣ መልካም ሚስትን፣ የአይን ማረፊያ የሆነ ልጅን፣ እረፍትን፣ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ስራንና የመሳሰሉትን ተወዳጅና ፍቁድ የሆኑ ተፈላጊዎችን ባጠቃላይ የዱንያ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በቀብር ውስጥ፣ በሒሳብ መቆሚያ ስፍራና በእሳት ውስጥ ከሚያጋጥም ቅጣቶች ሰላም መሆንን፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ ዘውታሪ ፀጋ መጎናፀፍን፣ አዛኝ ወደሆነው ጌታ መቅረብን የመሰሉ የመጨረሻው አለም መልካም ነገሮችንም የሚያጠቃልል ዱዓ ነው።