ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓ መካከል እርሳቸው እንዲህ ይሉ ነበር: (አልላሁመ ለከ አስለምቱ) ላንተ ታዛዥ ሆኛለሁ። (ወቢከ አመንቱ) ባንተ አረጋግጫለሁ፤ እውነት ብያለሁ። (ወዐለይከ ተወከልቱ) ባንተ ላይ ተደግፌያለሁ ተጠግቻለሁ። (ወኢለይከ አነብቱ) ወዳንተ ዞሬያለሁ፤ ተመልሻለሁ። (ቢከ ኻሶምቱ) ጠላቶችህን ተሟግቻለሁ። (አላሁመ ኢኒ አዑዙ) አላህ ሆይ እኔ እጠጋለሁ (ቢዒዘቲከ) ወደ ሀይልህና አሸናፊነትህ (ላኢላሃ ኢላ አንተ) ከአንተ ውጪ በእውነት የሚመለክ የለም። (አንቱዲለኒ) ወዳንተ ውዴታ ከመመራትና ከመገጠም እንዳታጠመኝ። (አንተል ሐይዩ ለዚ ላየሙት) የማይጠፋው ህያው ነህ። (ወልጂኑ ወልኢንሱ የሙቱን) ሰውና ጋኔን ይሞታሉ።