ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ መካከል "አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ።" ወደ አንተ እጠጋለሁ። "ከስንፍና" የሚጠቅመኝን መዘየድ ከማልችልበት "ከመታከት" የመስራት ፍላጎትን ከማጣት፤ ሰነፍ ማለት መዘየድ የማይችል ሲሆን መታከት ማለት ደግሞ መስራት አለመፈለግ ማለት ነው። "ከፈሪነት" መስራት ለሚገባኝ ወደ ፊት ከመሄድ ከመቆጠብ፤ "ከስስታምነት" መስጠት ግዴታዬ ከሆነ ከመሰሰት "ከእርጅና" ሰውነትን የሚያደክም ከሆነ መጃጀት "ከቀብር ቅጣት" እና ለቀብር ቅጣት ከሚዳርጉ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ። "አላህ ሆይ ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት!" መልካምን ለመስራትና ወንጀልን ለመተው ግጠማት። "ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት" ከአንተ ውጪ ነፍሴን የሚያፀዳ አንድም የለምና ነፍሴን ከውዳቂና ርካሽ ስነምግባር አፅዳት። "አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና።" የነፍሴን ጉዳይ የምትቆጣጠር፣ ጌታዋ፣ ባለቤቷና እርሷን የምትጣቅመው በአንተው ፀጋ ነውና። "አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ።" የኮኮብ እውቀት፣ የጥንቆላና የድግምት እውቀት አይነቱ ወይም ለመጪው አለም ከማይጠቅም እውቀት ወይም ከማይሰራበት እውቀት በአንተ እጠበቃለሁ። "አንተን ከማይፈራ ልብም በአንተ እጠበቃለሁ።" ለአንተ ከማይዋደቅ፣ ለአንተ የማይረጋ፣ አንተን በማውሳት ከማይረጋጋ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ከማትጠግብ ነፍስ" አላህ በሰጣትና ከለገሳት ጥሩና ሐላል ሲሳይ ከማትብቃቃ ነፍስ በአንተ እጠበቃለሁ። "ተቀባይነት ከሌላት" ተመላሽ ከሆነች "ዱዓም" በአንተ እጠበቃለሁ።"