ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓዎች መካከል ይህ ዱዓ ይገኝበታል: "አልላሁመ ኢንኒ አስአሉከል ሁዳ" አላህ ሆይ! ሐቅን የማወቅና በሐቅ የመስራት ቀጥተኛውን መንገድ እጠይቅሃለሁ። "ወትቱቃ" ትእዛዛቶችህን ለመተግበርና ክልከላዎችህን ለመራቅ የሚረዳኝን ፍራቻህን እጠይቅሃለሁ። "ወልዐፋፍ" ከማይፈቀዱና መልካም ካልሆኑ ንግግሮችና ተግባራት ጥብቅ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ። "ወልጊና" ከጌታዬ በቀር ወደ አንድም ፍጡር የማልፈልግ እስክሆን ድረስ ከፍጡራን የተብቃቃ እንድታደርገኝ እጠይቅሃለሁ።