ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአደም ልጆች ሁሉ ቀልባቸው እንደ አንድ ቀልብ ከአርረሕማን ጣቶች በሁለት ጣቶቹ መካከል መሆናቸውን ተናገሩ። እንደፈለገውም ይገለባብጠዋል። ከፈለገ በሐቅ ላይ ያፀናዋል፤ ከፈለገም ከሐቅ ያጠመዋል። በሁሉም ቀልቦች ላይ የሚፈፅመው ማስተናበር የአንድ ሰውን ቀልብ እንደማስተናበር ነው። አላህን አንድ ጉዳይ ከሌላ ጉዳይ አያጠምደውም። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀጥለው ይህን ዱዓ አደረጉ "አንዳንዴ ወደ ትእዛዝህ፣ አንዳንዴ አንተን ወደ መወንጀል፣ አንዳንዴ አንተን ወደማውሳት፣ አንዳንዴ ደሞ አንተን ከማውሳት ወደ መዘናጋት ቀልቦችን የምትገለባብጥ አላህ ሆይ! ልባችንን ወደ አምልኮህ አዙረው።"