ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነትና የእሳት ነዋሪዎችን አንዳንድ ባህሪያት ተናገሩ። አብዛኛው የጀነት ነዋሪዎች "ደካማና ዝቅ የሚደረጉ ናቸው።" ማለትም ለአላህ የሚተናነስና የሚዋደቅ፣ ነፍሱንም ለአላህ ዝቅ ያደረገ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዝቅ ያደርጉታልም ይንቁታልም። ይህ ለአላህ ብሎ ነፍሱን ዝቅ ያደረገ ሰው የአላህን ችሮታ ፈልጎ በአንድ ጉዳይ በአላህ ላይ ቢምል አላህ መሀላውን እውን የሚያደርግለት፤ የማለበትን ነገር የሚፈፅምለት፤ ፍላጎቱንና ዱዓውን የሚያሟላለት አይነት ሰው ነው። አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች "ልበ ደረቅ የሆነ ሁሉ" ይህ ቃል ደረቅ ለሆነ፣ አክርሮ ለሚሟገት ወይም መልካምን ለማይቀበል ባለጌ ሰው የሚውል ነው። "ትዕቢተኛ" (ጀዋዝ) ይህም ማለት ኩራተኛ፣ ሆዳም፣ ዝርፍጥ፣ ሲራመድ የሚንቦጣረርና መጥፎ ስነምግባር የተላበሰ ማለት ነው። "በኩራት የተሞላ" ማለት እውነትን ባለመቀበልና ሌላውን በመናቅ የሚኮራ ማለት ነው።