ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት የሚገባው የመጀመሪያው የአማኞች ህብረት ጨረቃ ሙሉ እንደምትሆንበት ምሽት ፊቶቻቸው እያበራ እንደሆነ፤ ከነርሱ ቀጥለው የሚገቡት ደግሞ ውበታቸው ሰማይ ላይ እንዳለ እጅግ ትልቅ ኮኮብ እንደሆነ፤ እንዲሁም የጀነት ሰዎች የተሟላ ባህሪያት እንዳላቸው ይህም የማይሸኑ፤ ሰገራ የማይወጣቸው፤ የማይተፉና የማይናፈጡ መሆናቸውን፤ ማበጠሪያቸውም ወርቅ፤ ላባቸው ሚስክ፤ ከእጣን ማጨሻቸው የሚወጣው መአዛ ምርጥ መአዛ ያለው እጣን እንደሆነ፤ ሚስቶቻቸው ሑሩል ዒን ናቸው። በአፈጣጠርና ቁመትም ልክ እንደ አንደሰው የአባታቸውን አደም ቅርፅ ይዘው እንዳላቸውና የአደም ሰውነት ርዝማኔም ስልሳ ክንድ እንደሆነ ተናገሩ።