ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ጀነትና እሳትን እነደፈጠራቸው ለጂብሪል ዐለይሂ ሰላም እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "ወደጀነት ሂድና ወደርሷ ተመልከት!" ጂብሪልም ሄዶ ወደርሷ ተመልክቶ ተመለሰ። ጂብሪልም እንዲህ አለ:- "ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! በውስጧ ስለሚገኘው ፀጋ፣ መከበሪያና መልካም ነገሮች ማንም ቢሰማ ወደርሷ መግባት የሚወድና ስለርሷም ከመስራት አይታቀብም።" በማለት መለሰ። ከዚያም አላህ ጀነትን ለነፍስ የሚከብዱና አስቸጋሪ በሆኑ ትእዛዛቶችን በመፈፀምና ክልከላዎችን በመራቅ ከበባት። ይህም ወደ ጀነት መግባት የፈለገ ይህን አስቸጋሪ መንገድ ማለፍ እንዲጠበቅበት ነው። ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ ለነፍስ በሚከብዱ ነገሮች ከከበባት በኋላ እንዲህ አለ፦ " ጂብሪል ሆይ! ወደ ጀነት ሂድና ተመልከታት!" ሄዶ ወደርሷ ተመልክቶ በመምጣት እንዲህ አለ፦ " ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! ወደርሷ በሚያደርገው ጉዞ በሚያጋጥሙት ችግሮችና መከራዎች ምክንያት ማንም አይገባትም ብዬ እፈራለሁ።" አላህ እሳትን የፈጠረ ጊዜ፦ "ጂብሪል ሆይ! ሂድና ወደርሷ ተመልከት" አለው። ወደርሷ ሂዶም ተመለከተ። ከዚያም በመምጣት እንዲህ አለ፦ "ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! ውስጧ ስላለው ቅጣትና ጭንቀቶች አንድም አይሰማም ውስጧ መግባትን በመጥላት ወደርሷ ከሚያስገቡ ምክንያቶችም የራቀ ቢሆን እንጂ።" ከዚያም የተከበረውና የላቀው አላህ እሳትን ከበባት፤ ወደርሷ መድረሻ መንገድንም ለነፍስ የሚያስደስትና የሚያረካትን ነገሮች አደረገ። ከዚያም "ጂብሪል ሆይ! ሂድና ወደርሷ ተመልከት " አለው። ጂብሪልም ወደርሷ ሂዶ ተመልክቶ በመምጣት እንዲህ አለ፦ " ጌታዬ ሆይ በልቅናህ እምላለሁ! በዙሪያዋ ባሉት ለነፍስ አርኪና አስደሳች ነገሮች ምክንያት በርግጥም ከሷ አንድም አይድንም ብዬ ሰጋሁ፤ ፈራሁ።"