ጣዉስ እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች የሆኑ ሰዎችን አግኝቻለሁ። "ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ ነው"ይሉም ነበር። ጣዉስ እንዲህም አሉ፦ " ዐብደላህ ቢን ዑመርን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁሉም ነገር በአላህ ውሳኔ መሆኑን ገለፁ። ስንፍና ሳይቀር ተወስኗል: እሱም: - ዱንያዊና አኺራዊ ከሆኑ ጉዳዮች መስራት ግድ የሆነበትን ነገር መተው፣ ሳይሰሩ መገኘት ፣ ከወቅቱ ማዘግየት ነው። ጮሌነት ሳይቀር ተወስኗል: እሱም:- ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳዮችን ለመስራት መነቃቃትና ብልህ መሆን ማለት ነው። የላቀውና የተከበረው አላህ ስንፍናና ጮሌነትን ሳይቀር ሁሉንም ነገር ወስኗል። በዚህ ዓለም የአላህ ዕውቀትና ፍላጎት የቀደመው ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አይከሰትም።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በአላህ ውሳኔ (ቀደር) ጉዳይ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እምነት መገለፁ።
  • ስንፍናና ንቁነት ሳይቀር ሁሉም ነገር የሚከሰተው በአላህ ውሳኔ መሆኑን፤
  • የአላህ መልክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሐዲሥ በማስተላለፉ ረገድ የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ጥንቃቄና ማረጋገጥ፤
  • በመልካሙም ሆነ በመጥፎው ሁሉም ጉዳይ በአላህ ውሳኔ መሆኑን ማመንን ተረድተናል።