ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚጋልቡበት ተፈናጥጦ ሳለ ለሱ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል: እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አስተምርሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎችህ የአላህ ጥበቃ የማይለይህና ወደየትም ብትዞርም የቸገረህን በመርዳት አላህ የሚጠብቅህ ትሆናለህ። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! ለጠያቂዎች ልመና ምላሽ የሚሰጠው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማያደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም። የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውን በመራቅ አላህን የጠበቀ ሰው አላህ ባሪያው ያለበትን ሁኔታ ያውቃልና እርሱን በመርዳትና በማገዝ ከፊትለፊቱ ይሆናል። ሰው በድሎት ወቅት አላህን ከታዘዘ አላህም በጭንቁ ወቅት ስኬትና መውጫ መንገድን ያበጅለታል። ሁሉም ሰው አላህ በወሰነለት መልካምም ይሁን መጥፎ ነገር መውደድ አለበት። ከችግሮችና ፈተናዎች ጋርም አንድ ባሪያ ትእግስትን መያዝ አለበት። ትእግስት የስኬት ቁልፍ ነው። ችግር በበረታ ወቅት ከአላህ የሆነ ስኬት ይመጣል። አላህ ችግርን ሲያመጣ ድሎትንም ያስከትልበታል።