ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሲገቡ እቃ የምታስቀምጥበትን ትንሽዬ ክፍል ነፍስ ያላቸው ምስሎች ባለበት መጋረጃ ሸፍናው አገኟት። የፊታቸው ቀለምም ለአላህ ብለው በመቆጣታቸው ምክንያት ተለዋውጦ መጋረጃውን አወለቁት። እንዲህ አሉ: የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት የአላህን ፍጥረት አስመስለው ምስል የሚያደርጉት ናቸው። ዓኢሻም እንዲህ አለች: እርሱን አንድ ትራስ ወይም ሁለት ትራስ አደረግነው።