ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ እጅግ ትልቁ ወንጀል ተጠየቁ: እጅግ ትልቁ ወንጀል ትልቁ ሺርክ ነው። እርሱም ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ ምሳሌ ወይም ቢጤን ማድረግክ ነው። ይህን ወንጀል አላህ ያለ ተውበት አይምረውም። ባለቤቱ በዚህ ወንጀል ላይ ሳለ ከሞተም በእሳት ውስጥ ዘውታሪ ነው። ቀጥሎም ሰውዬው ልጁን ከርሱ ጋር መብላቱን ፈርቶ መግደሉ ነው። በመሰረቱ ነፍስን መግደል ክልክል ነው። ነገር ግን ተገዳዩ የገዳዩ ዘመድ ከሆነ ወንጀሉ የከፋ ይሆናል። አሁንም በድጋሚ ገዳዩ የመግደሉ አላማ ተገዳዩ በአላህ ሲሳይ ላይ እንዳይጋራው አስቦ ከሆነ ወንጀሉ እጅግ የከፋ ይሆናል። ቀጥሎ አንድ ሰው በጎረቤቱ ሚስት ላይ ዝሙት መስራቱ ነው። እርሷ ላይ ዝሙት እስኪሰራና ታዛዡ እስክትሆን ድረስ የጎረቤቱን ሚስት ለማታለል መሞከሩ ነው። በመሰረቱ ዚና ክልክል ነው። ነገር ግን ዝሙት የተሰራባት ሸሪዓ ለነርሱ መልካም እንድንውልላቸው፣ በጎ እንድናደርግላቸውና ጥሩ ወዳጅነት እንዲኖረን ያዘዘን በሆኑት የጎረቤት ሚስት ከሆነች ወንጀሉ የከፋ ይሆናል።