ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አለ፦ በንግግራቸው እውነተኛ የሆኑትና አላህ እውነተኛነታቸውን በማረጋገጡ እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነገሩን: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ፍጥረቱ ይሰበሰባል" ይህም አንድ ወንድ ባለቤቱን የተገናኘ ጊዜ የተበታተነው ዘር ፈሳሹ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ለአርባ ቀን የዘር ፈሳሽ ሆኖ ይሰበሰባል። ከዚያም የረጋ ደም ይሆናል። ይህም የደረቀ ወፍራም ደም ነው። ይህ በሁለተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ቁራጭ ስጋ ይሆናል። ይህም የሚታኘክ የሚያህል ቁራጭ ስጋ ነው። ይህ በሶስተኛው አርባ የሚከሰት ነው። ከዚያም ወደርሱ አላህ መልዐክ ይልካል። ሶስተኛው አርባ ከተጠናቀቀ በኋላ ፅንሱ ውስጥ ሩሕ (ነፍስ) ይነፋበታል። መልዐኩ አራት መልእክቶችን እንዲጽፍ ይታዘዛል። እነሱም:- ሲሳዩን: ይህም በእድሜው ውስጥ ምን ያህል መጠን ነው የሚያገኘው ፀጋ የሚለውን ነው። የሞት ቀጠሮውን:- ይህም በዱንያ ውስጥ የሚቆይበትን ዘመን ነው። ሥራውን:- ምንድነው እሱ? እድለቢስ ነው ወይስ እድለኛ? ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ማሉ። አንዱ የጀነት ሰዎችን ሥራ ይሠራል፤ ሥራው ለሰዎች በሚታየው መልካም ይሆናል፤ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል እስኪቀር በዚው መልክ ይቀጥላል። ማለትም አንድ ያሰበው ቦታ ለመድረስ አንድ ክንድ እንደቀረው ሰው በርሱና ጀነት በመግባት መካከልም አንድ ክንድ በስተቀር ምንም አይቀርም። በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና በዛን ወቅት የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራና በዛው ላይ ፍፃሜው ይሆናል። እሳትም ይገባል። ሥራ ተቀባይነት እንዲያገኝ አንዱ መስፈርት በዛው ላይ መፅናትና አለመለወጥ ነውና። ከሰዎች ሌላኛው ደግሞ እሳት ለመግባት በርሱና በእሳት መካከል የምድር አንድ ክንድ ያህል የቀረው እስኪመስል ድረስ የእሳት ባለቤቶችን ሥራ ይሠራል፤ በርሱ ላይ የተወሰነው መጽሐፉ ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።