ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለዐጧእ ቢን አቢረባሕ እንዲህ አሉ: "የጀነት ነዋሪ የሆነችን ሴት አላሳይህምን?" ዐጧእም "እንዴታ!" አለ። ኢብኑ ዐባስም እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሐበሻዊት ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: "የሚጥል በሽታ ስላለብኝ ይጥለኝና እገላለጣለሁኝ። ታዲያ እኔ ሳላውቀው ከሰውነቴ የተወሰነው ክፍል ይገለጣል። አላህ ጤናን እንዲለግሰኝ ለምኑልኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ጤናን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁኝ።" እርሷም እንዲህ አለች: "እንዲህ ከሆነ እታገሳለሁኝ። አክላም "ስወድቅ እንዳልገላለጥ ግን አላህን ይለምኑልኝ።" አለች። እርሳቸውም አላህን ለመኑላት።