explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱንያም ውስጧ ያሉ ነገሮችም በሙሉ ጊዜያዊ መጠቀሚያዎች ሆነው ከዚያም የሚጠፉ መሆናቸውን፤ በላጩ መጣቀሚያም ሲያያት የምታስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ ሲርቅ ነፍሷንና ንብረቱን የምትጠብቅ መልካም ሚስት መሆኗን ተናገሩ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አላህ ለባሮቹ ፍቁድ ባደረጋቸው የዱንያ መልካም ነገሮች ላይ ያለማባከንና ያለመኩራራት መጠቀም መፈቀዱን እንረዳለን።
  • ባል በጌታው አምልኮ ላይ የምታግዘው መልካም ሚስት እንዲመርጥ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  • ከዱንያ መጣቀሚያዎች ሁሉ ምርጡ አላህን በማምለክ ላይ የሆነ ወይም አላህን በማምለክ ላይ አጋዥ የሆኑ ነገሮች መሆኑን እንረዳለን።