ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንግዳ ሴቶች ጋር ከመቀላቀል እንዲህ በማለት አስጠነቀቁ "በሴቶች ላይ ከመግባትና ሴቶችም እናንተ ዘንድ እንዳይገቡ ነፍሳችሁን ጠብቁ!" አንድ የአንሷር ሰውዬም እንዲህ አለ: እስኪ ንገሩኝ የባል ወንድም፣ የወንድሙ ልጅ፣ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ የእህቱ ልጅና የመሳሰሉት ባታገባ ኖሮ ልታገባቸው የሚፈቀዱላት የባል ቅርብ ዘመዶች ቢገቡስ ይፈቀዳልን? ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "ሞትን እንደምትጠነቀቁት እርሱንም ተጠንቀቁት! ከባል ዘመዶች ጋር ገለል ብሎ ማሳለፍ ለሃይማኖት ፈተናና ጥፋት የሚመራ ነው። ከአባቱና ከልጆቹ ውጪ ያሉ የባል ቅርብ ዘመዶችን መከልከል ከሌላው ባዳ ወንድ የበለጠ የተገባ ነው። ይህም ከሌላ ባዳ ጋር ለብቻ ከምታሳልፍበት ጊዜ ይልቅ ከባል ቅርብ ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ እድሉ የበዛ ስለሆነ ከሌላው በበለጠ ከርሱ ጋር መጥፎ ነገር መከሰቱ ስለሚገመትና ያለምንም አውጋዥ ወደ ሴቷ መድረስና ከርሷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ስለሚችል ፈተና የመከሰት እድሉም የሚመች ነው። በተለምዶ የባል ወንድም የወንድሙ ሚስት ብቻዋን እያለች መግባት ቸል የሚባል ጉዳይ ስለሆነ ፈተና መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከባዳ ወንድ ጋር ለብቻ ማሳለፍማ የሚጠነቀቁት ጉዳይ ነው። ከርሱ በተቃራኒ ከባል ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ አፀያፊነትና የሚያስከትለው ችግር ግን ከሞት ጋር ይመሳሰላል።