ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱንያ ስትቀመስ ጣፋጭ ስትታይ ደግሞ አረንጓዴ ለምለም ስለሆነች ሰው በርሷ እንደሚሸወድ፣ በርሷ እንደሚሰምጥና ትልቁ ግቡ እንደሚያደርጋትም ገለፁ። ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በዚህች የዱንያ ህይወት እንዴት እንደምንሰራና ለርሱ ታዛዥ እንሆናለን? ወይስ እናምፀዋለን? የሚለውን ለመመልከት ከፊላችን ከፊሉን እንዲተካ አድርጓል። ከዚያም: "የዱንያ መጣቀሚያና ጌጧ እንዳይሸውዳችሁ፤ አላህ ያዘዛችሁን ለመተውና በከለከላችሁ ላይ ለመውደቅ እንዳያነሳሳችሁ ተጠንቀቁ! አሉ። እጅግ ትልቁ ከዱንያ ፈተናዎች መካከል መጠንቀቅ ግድ የሚሆንብንም የሴቶች ፈተና ነው። ሴት በኒ ኢስራኢሎች የወደቁበት የመጀመሪያዋ ፈተና ናት።"