ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ጥፍጥናን ቆራጩን ማስታወስ አብዙ።" ሞትን ማለታቸው ነው። ሐሰን ነው። - رواه الترمذي والنسائي وابن ماجه
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሰው ልጅ እርሱን ሲያስታውሰው የመጪው ዓለምን የሚያስታውስበትንና ለዱንያ ጥፍጥና በተለይ ደሞ ክልክል ለሆኑ መጣቀሚያዎች ያለውን ፍቅር ከቀልቡ የሚያጠፋለትን ሞትን አብዝቶ እንዲያስታውስ አነሳሱ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • ሞት የዱንያን ጥፍጥና ይቆርጣል። ነገር ግን አማኝ የሆነን ሰው ወደ መጪው አለም ጥፍጥና፣ ወደ ጀነት ደስታና በጀነት ውስጥ ወደሚገኝ ትልቅ መልካም ነገር ነው የምታሸጋግረው።
  • ሞትንና ከሞት በኋላ ያለውን ህይወት ማስታወስ የተውበት፣ ከወንጀል የመውጣትና ለመጪው አለም የመዘጋጀት ሰበብ ነው።