ከኑዕማን ቢን በሺር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "እናንተ የምትፈልጉትን ምግብና መጠጥ እየተመገባችሁ አይደልንዴ? ነቢያችሁን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሆዳቸውን የሚሞሉበት የሆነ የወረደ ተምርን እንኳ ሳያገኙ ቀርተው ተመልክቻቸዋለሁ።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።