ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "እስልምና ላይ ሆኖ የሚበቃውን ያህል ሲሳይን የተለገሰና አላህ በሰጠውም የተብቃቃ ሰው በርግጥም ስኬታማ ሆኗል።" ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።