አንድ ቀን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦቻቸውን ለማናገር ሚንበር ላይ ተቀመጡና እንዲህ አሉ: ከኔ በኋላ በናንተ ላይ እጅግ አብዝቼ የምፈራላችሁ ነገር ቢኖር ለጥቂት ጊዜ የሚቆይ ከመሆኑም ጋር ለናንተ የሚከፈትላችሁን የምድር በረከት፣ የዱንያ ጌጥና ውበት፣ በውስጧ ያለውን የልብስ፣ የአዝርዕትና ሌሎችም ሰዎች በውበቱ የሚፎክሩበት የመጣቀሚያ አይነቶችን ነው። አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: የዱንያ ውበት የአላህ ፀጋ ነው። ይህ ፀጋ ታዲያ ወደ ቅጣትና መዐትነት ይለወጣል ማለት ነውን? ሰዎች የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዝምታ ሲመለከቱ አስቆጥቷቸዋል ብለው በማሰብ ጠያቂውን ወቀሱት። በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ወሕይ እየወረደ እንደነበር ግልፅ ሆነላቸው። ቀጥለውም ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠረጉ ጠያቂው የት አለ? አሉ። እርሱም "እኔ ነኝ!" አለ። አላህን አመሰግነው በርሱም ላይ ካወደሱ በኃላ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ትክክለኛ መልካም ነገር መልካሙን እንጂ ሌላ ነገር ይዞ አይመጣም። ነገር ግን ይህቺ የዱንያ ውበት ወደ ፈተና፣ እሽቅድድም፣ ወደ መጪው አለም ሙሉ ለሙሉ ከመዞር ስለምታጠምድ ጥርት ባለ መልኩ መልካም አይደለችም። ቀጥለው እንዲህ በማለት ለዚህ ምሳሌን ጠቀሱ "የፀደይ ቡቃያና አትክልት እንስሶች ለመጋጥ የሚወዱት ስለሆነ አብዝተው በመብላታቸው በቁንጣን ይገላቸዋል፤ ወይም ወደ ሞት ያቀርባቸዋል። ይህ ግን የሆዷ አንድ ጎን እስኪሞላ አትክልቱን ግጣ ቀጥላ ወደ ፀሃይ ዞራ ከሆዷ ቀጭን ሰገራዋን አውጥታ ወይም ሸንታ ሆዷ የገባውን መልሳ አውጥታ አመንዥካ ድጋሚ የምትውጥ ከዚያም ተመልሳ የምትግጥ እንስሳን አይገድላትም። አሉ። ይህ ገንዘብም እንደ ጣፋጭ አትክልትና ቡቃያ ነው። በሐላል መንገድ አግኝቶት በሚያስፈልገው ያህልና በቂውን በሚያገኝበት ብቻ በጥቂት ገንዘብ ላይ የተብቃቃ ሲቀር ከበዛ ይገድላል ወይም ለመግደል ይቀርባል። የሚያስፈልገውን ብቻ ከሆነ የሚጠቀመው አይጎዳውም። ለሚስኪኖች፣ ለየቲሞችና ለመንገደኞች የሚሰጥ ሙስሊም ሰው ምንኛ ያማረ ነው! ገንዘብን በአግባቡ የሚይዝ ይባረክለታል። ያለአግባብ የሚይዘው ደግሞ የርሱ ምሳሌ እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። በርሱ ላይም የትንሳኤ ቀን ይመሰከርበታል።