ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአራት ጉዳዮች ከለከሉ። የመጀመሪያው: ሴት ልጅን ያለባሏ ወይም ያለ አንድ ዘመዷ ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድ ከመጓዝ መከልከል ነው። ዘመዷ የተባሉትም እንደ ልጅ፣ አባት፣ የወንድም ልጅ፣ የእህት ልጅ፣ አጎትና የመሳሰሉት ያሉ ለዘላለም በነርሱ ላይ ለጋብቻ እርም የተደረገችባቸው ቅርብ ዘመዶቿ ናቸው። ሁለተኛው: የዒደል ፊጥርና የዒደል አድሓ ቀንን የመፆም ክልክልነት ነው። በነዚህ ቀናቶች ላይ አንድ ሙስሊም ለስለትም ወይም ለበጎ ፍቃደኝነትም ወይም ለማካካሻ ብሎም መፆሙ ክልክል ነው። ሶስተኛው: ከዐስር ሶላት በኋላ ፀሀይ እስክትገባ ድረስና ጎህ ከቀደደ በኋላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ሱና ሶላትን ከመስገድ መከልከሉ ነው። አራተኛው: ከነዚህ ሶስት መስጂዶች በቀር ወደ ማንኛውም ስፍራ ወደርሱ የመጓዝን ብልጫ አስቦ፣ በመጓዝ ምክንያትም ምንዳ ይነባበራል ብሎ በማመን መጓዝ መከልከላቸው ነው። ከነዚህ ሶስት መስጂዶች በቀርም በውስጧ ለመስገድ በሚል ጓዝ ተሸክፎ አይኬድም። ከነዚህ ሶስት መስጊዶች በቀርም ምንዳ አይነባበርም። እነሱም: መስጂደል ሐራም፣ የነቢዩ መስጂድና መስጂደል አቅሷ ናቸው።