explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በፍጡራኖች ላይ የሚከሰተውን ውሳኔዎች ህይወት፣ ሞት፣ ሲሳይና ሌሎችንም ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት በዝርዝር በጥብቅ ሰሌዳ ውስጥ እንደፃፈውና እሱም አላህ በወሰነው መልኩ የሚከሰት መሆኑን ተናገሩ። ሁሉም የሚከሰቱ ነገሮች በአላህ ፍርድና ውሳኔ መሰረት ነው። አንድ ሰውን ያገኘው ነገር ቀድሞውኑ ሊስተው አይችልም ነበር፤ የሳተውም ነገር ሊያገኘው አይችልም ነበር።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በአላህ ፍርድና ቅድመ ውሳኔ ማመን ግዴታ መሆኑን እንረዳለም።
  • ቀደር (ውሳኔ) ሲባል :- አላህ በነገሮች ላይ ያለውን ዕውቀት፣ መፃፉን፣ መሻቱንና መፍጠሩን የሚያጠቃልል ነው።
  • ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ውሳኔዎች እንደተፃፉ ማመን በሚያጋጥሙን ነገሮች መውደድና መቀበልን ይፈይደናል።
  • ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የአርረሕማን ዐርሽ ውኃ ላይ ነበር።