ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እየጋለበ ሳለ ለሱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል : እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አሳውቅሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎች የአላህ ጥበቃና ወደየትም ብትዞር የቸገረህን በመርዳት አላህም የሚጠብቅህ ይሆናል። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! የጠያቂዎችን ልመና የሚቀበለው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማይደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም።