ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅና ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ አብራሩ። አላህ ባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ እሱን ብቻ ሊያመልኩና በሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው። ባሮች በአላህ ላይ ያላቸው ሀቅ ደግሞ እነዚያ በሱ ላይ አንዳችንም ሳያጋሩ በብቸኝነት ያመለኩትን ላይቀጣ ነው። ቀጥሎ ሙዓዝ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሰዎች በደስታ እንዲበሰሩ በዚህ የላቀ የአላህ ትሩፋት ላበስራቸውን?" አለ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሷ ላይ መደገፋቸውን ፈርተው እንዳያበስራቸው ከለከሉት።