ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይና አቡ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድን ሙስሊም ድካም፣ በሽታ፣ ሀሳብ፣ ሀዘን፣ ጉዳት፣ ጭንቀት የምትወጋው አንዲት እሾክ እንኳ (በከንቱ) አታገኘውም አላህ በሷ ምክንያት ከወንጀሎቹ የሚምርለት ቢሆን እንጂ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።