ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአላህ ዘንድ ያላቸውን ደረጃ አሳወቁ፤ ልክ እንደ ኢብራሂም ዐለይሂ ሰላም እሳቸውም ላእላይ እርከን የደረሰ ውዴታ መጎናፀፋቸውንም ተናገሩ። ልባቸው በአላህ ውዴታ፣ ማላቅና ማወቅ ስለተሞላ ከአሏህ ውጭ ፍፁም ወዳጅ ሊኖራቸው እንደማይችልም ገለፁ። ከፍጡራን መካከል ፍፁም ወዳጅ የሚይዙ ቢሆኑ ኖሮ ያ ሰው አቡበከር አስሲዲቅ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና ይሆን እንደነበረም ተናገሩ። ከዚያም አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነቢያቶቻቸውንና የፃድቃኖቻቸውን መቃብር ከአላህ ውጪ ወደምትመለክ ጣኦታዊ የአምልኮ ስፍራ በመለወጥ እንዲሁም የፃድቃኖችና ነቢያቶች መቃብር ላይ መስገጃና ቤተ መቅደሶችን በመገንባት የፈፀሙትን ልክ ያለፈ የውዴታ ድንበር ከማለፍ አስጠነቀቁ። አስከትለውም ኡመታቸውም የነሱን አይነት ድርጊት እንዳይፈፅሙ ከለከሉ።