ከበራእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል።"» ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።