አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመምጣት (አስሰላሙ ዐለይኩም) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለት። ቀጥሎም ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ አስር ምንዳ ተጽፎለታል አሉ። ከዚያም ሌላ ሰው መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ) አላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሀያ ምንዳ አለው አሉ። ከዚያም ሌላ ሰውዬ መጣና (አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ) አላቸው። ሰላምታውን መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለርሱ ሰላሳ ምንዳ አለው አሉ። ማለትም እያንዳንዱ ቃል አስር ምንዳ ያስገኛል ማለታቸው ነው።