ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልዕክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'" በቡኻሪ ዘገባ ደግሞ "ህፃን ለትልቅ ሰላምታን ያቅርብ፤ ተጓዥ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች ለብዙ ሰዎች ሰላምታን ያቅርቡ።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።