ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ወንድሙን ያገኘ ጊዜ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ! በመካከላቸው ዛፍ ወይም ግድግዳ ወይም ድንጋይ ከጋረዳቸው በኃላም ድጋሚ ቢያገኘው በድጋሚ በርሱ ላይ ሰላምታን ያቅርብ።" ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ ዘግበውታል።