explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ላይ ያለውን ጥቂት መብቶች ገለፁ። ከነዚህ መብቶች መካከል የመጀመሪያው ሰላምታ ለሰጠህ ሰላምታን መመለስ ነው። ሁለተኛው መብት፡ ህመምተኛን መጠየቅና መዘየር ነው። ሶስተኛው መብት፡ ጀናዛን ከቤቱ ወደ ሚሰገድበት ከዚያም ወደ መቃብሩ ተወስዶ እስኪቀበር ድረስ መሸኘት ነው። አራተኛው መብት፡ ለሰርግም ይሁን ለሌላ ግብዣ ሲጠራ ጥሪውን አክብሮ ምላሽ መስጠት ነው። አምስተኛ መብት፡ ሲያስነጥስ "ተሽሚት" ሊያደርግ ሲሆን ይኸውም አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው) ካለ "የርሐሙከሏህ" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይዘንልህ) ይበለው፤ ከዚያም ያስነጠሰውም መልሶ "የህዲኩሙሏሁ ወዩስሊሕ ባለኩም" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይምራህ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) ይላል።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • እስልምና በሙስሊሞች መካከል ያሉ መብቶችን በማበርታትና በመካከላቸው ያለን ወንድማማችነትና መዋደድን በማጠናከር በኩል ያለውን ልቅና ያስረዳናል።