ነቢዩ(የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሽተኛን የጠየቁ ጊዜ እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉለት ነበር: አላህ ሆይ! (አዝሂብ) አስወግድ (አልባስ) የበሽታውን ሀይለኝነት (ረብበ ናስ) የሰዎች ፈጣሪና ተንከባካቢ የሆንከው! (ወሽፊ) ይህን በሽተኛ ፈውሰው (አንተ ሻፊ) ጥራት ይገባህና "አሽ‐ሻፊ" (ሁሉንም ፈዋሽ) በሚለው ስምህ ወዳንተ እቃረባለሁ። (ላሺፋአ) ህመምተኛ ላጋጠመው በሽታ ፈውስ የለም (ኢላ ሺፋኡክ) ከአንተ ፈውስ በቀር። (ሺፋአን) አጠቃላይ ፈውስን ስጠው (ላዩጋዲሩ) የማይተውና የማያስቀር የሆነን (ሰቀማ) ሌላን በሽታንም።