ዑሥማን ቢን አቢልዓስን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሊገድለው የቀረበ የሆነ በሽታ አጋጥሞት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሊጠይቁት መጡ። አላህ ያረፈበትን በሽታ እንዲያስወግድለት የሚያደርግ ዱዓንም አስተማሩት። ይሀውም የሚያመው ስፍራ ላይ እጁን በማድረግ ሶስት ጊዜ (ቢስሚላህ) ማለት ቀጥሎም ሰባት ጊዜ ይህንን ማለት (አዑዙ) እጠጋለሁ፣ እጠበቃለሁ (ከሚሰማኝ ክፋት በአላህና በችሎታው) አሁን ላይ ከሚያመኝ ህመም ማለት ነው። (ከምፈራው) ለወደፊት ከሚያገኘኝና ከምፈራው ሀዘንና ፍርሃት ወይም ይህ በሽታ ከመቀጠሉና ህመሙ በሰውነቴ ውስጥ ከመሰራጨቱ በአላህ እጠበቃለሁ ማለት ነው።