መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ወደ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በመምጣት ጠየቃቸው: "ሙሐመድ ሆይ! በህመም ተጠቃህን?" እርሳቸውም: "አዎ" አሉ። ጂብሪልም ነቢዩን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጥበቃ አደረገላቸው: "ቢስሚላሂ" በአላህ ስም ታግዤ "አርቂከ" እጠብቅሃለሁ። "ሚን ኩሊ ሸይኢን ዩእዚከ" ትንሽም ሆነ ትልቅ ከሚያውክህ ነገር ሁሉ እጠብቅሃለሁ። "ሚን ሸሪ ኩሊ ነፍሲን አው ዓይኒን ሓሲድ" ከሁሉም ክፉ ነፍስ ወይም ምቀኛ አይን እንዳያገኝህ እጠብቅሃለሁ። "አሏሁ የሽፊከ" አላህ ከሁሉም በሽታ እንዲፈውስህና እንዲጠብቅህ "ቢስሚላሂ አርቂከ" በአላህ ስም እጠብቅሃለሁ። ("ቢስሚላሂ አርቂክ" የሚለውን) ሁለቴ የደጋገመውና በርሱ ጀምሮ በርሱ ያጠናቀቀው ከአላህ ውጪ ማንም እንደማይጠቅም ለመጠቆም ነው።