ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው። ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።