ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።» ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ: መጀመሪያ: ከአፋቸው ወይም ከአፍንጫቸው አንዳች ነገር ወጥቶ አብሯቸው የተቀመጠውን ላለማወክ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ ያኖራሉ። ሁለተኛ: ድምፃቸውን ይቀንሱ ነበር። ከፍም አያደርጉትም።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • በማስነጠስ ዙሪያ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መመሪያ መገለፁና በዚህ ጉዳይ እርሳቸውን መከተል እንደሚገባ እንረዳለን።
  • አንድ ሰው ያስነጠሰ ጊዜ ከርሱ አንዳች ነገር ወጥቶ አብሮ የተቀመጠውን እንዳያውክ ልብስን ወይም መሀረብና የመሳሰሉትን አፍና አፍንጫ ላይ ማኖር እንደሚወደድ እንረዳለን።
  • ሲያስነጥሱ ድምፅን ዝግ ማድረግ የሚፈለግ ጉዳይ ነው። ይህም ስነ-ስርዓትን ከሚያሟሉና ከመልካም ስነ‐ምግባር የሚመደብ ነው።