ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ወንድሙ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ስድስቱን ጠቀሱ፡ የመጀመሪያው: ባገኘው ጊዜ "አስሰላሙ ዐለይኩም" (ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን) በማለት ሰላምታውን ያቅርብለት። እርሱም "ወዐለይኩሙ-ስሰላም" በማለት ሰላምታውን ይመልስለት። ሁለተኛው: ለሰርግና ለሌሎች ድግሶች በጠራው ጊዜ ጥሪውን ማክበር ነው። ሶስተኛው: ምክር ባስፈለገው ጊዜ ያለምንም ማሞኘትና ማታለል መምከር ነው። አራተኛው: አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው) ያለ ጊዜ "የርሐሙከላህ" (አላህ ይዘንልህ፤ ይቅር ይበልህ) በማለት አስደስተው። እርሱም "የህዲኩሙሏህ ወዩስሊሕ ባለኩም" (አላህ ይምራህ፤ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) በማለት ይመልስ። አምስተኛው: በታመመ ጊዜ ይጠይቀው፤ ይጎብኘው። ስድስተኛው: በሞተ ጊዜ ይስገድበት፤ እስኪቀበር ድረስም ጀናዛውን ይከተለው።