ከአቡ ሲርመህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።" ሐሰን ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።