ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።" ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።