ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን አንዱ ሌላኛውን በሚያገኘው ጊዜ ሰላምታም ሳይሰጠውና ሳያናግረው ከሶስት ሌሊቶች በላይ ማኩረፍን ከለከሉ። ከነዚህ ሁለት ጠበኞች መካከል በላጩ ኩርፊያውን ለማስወገድ የሚሞክርና ሰላምታ የሚጀምረው ነው። እዚህ ሐዲስ ውስጥ ኩርፊያ በማለት የተፈለገው በነፍሱ ፍላጎቶች ያኮረፈ ከሆነ ነው። ወንጀለኞችን፣ የቢድዓ ባለቤቶችንና መጥፎ ጓደኞችን የመሰሉ ሰዎችን ለአላህ ሀቅ ብሎ ማኩረፍ ከሆነ ግን በወቅት ሳይሆን የሚገደበው ኩርፊያው በሚያመጣው ጥቅምና ያለባቸው ችግር በመወገዱ ላይ ነው የሚገደበው።